ነሲሓ አካዳሚ

ስለ ነሲሓ አካዳሚ ምን ያውቃሉ?

وَقُلْ رَبِّ زِدْنِي عِلْمًا

«ጌታዬ ሆይ! ዕውቀትንም ጨምርልኝ» በል፡፡

አካዳሚ "ኢስላማዊ ዕውቀት ለሁሉም" በሚል መሪ ቃል በነሲሓ ቲቪ የሚተላለፉ ተከታታይ ትምህርቶች ላይ የተመረኮዘ መርሃ ግብር ሲሆን ትምህርቱ ሁለት አይነት እርከኖች አሉት:‐
  1. 1) መሰረታዊ የዲን ትምህርት ለሁሉም
  2. ይህ ለጀማሪዎች እንዲስማማ የተቀረፀ መርሃ ግብር ሲሆን በውስጡም:‐ የተፍሲር፣ የሐዲሥ፣ የፊቅህ፣ የተዉሂድ፣ የሲራ፣ የዐረብኛ ቋንቋ እና የተርቢያ ዘርፎችን ያካተተ ይሆናል። ትምህርቶቹን ከተከታተሉ የማጠናቀቂያ ፈተና ወስደው ሰርተፊኬት የሚያገኙበት ልዩ የትምህርት መርሐ–ግብር ነው።

2) ነሲሓ ተከታታይ የኪታብ ቂራአት ይህ እረከን የተለያዩ እውቅ ኪታቦችን መማር የሚሹ ተማሪዎችን (ጠለበተል—ዒልም) ን ታሳቢ ያደረገ ነው። በተለያየ ግዜ የሚተላለፉ የኪታብ ቂራአት ፕሮግራሞች ሲጠናቀቁ፤
  • √ ማንኛውም ተማሪ በአካዳሚው ለዚህ ትምህርት የሚሰጠውን ፈተና በመውሰድ በተማረው ኪታብ ላይ የተገደበ የተሳትፎ የምስክር ወረቀት ያገኛል።
  • √ የተለያዩ ኪታቦችን በርቀት በመማር ነጥቦችን አጠራቅሞ የነሲሓ አካዳሚን የዲፕሎማ መስፈርት እንደሚያሟላ ከተረጋገጠ የዲፕሎማ ሰርተፊኬት ፈተናዎችን በመውሰድ እንደውጤቱ የዲፕሎማ ሰርቲፊኬት ያገኛል።
የነሲሓ አካዳሚ ቋሚ ተመሪዎች መመዝገቢያ ይህንን የመመዝገቢያ ቅፅ በመሙላት የነሲሓ አካዳሚ ቋሚ ተማሪ ሆነው ሲመዘገቡ ለትምህርቱ አጋዥ የሆኑ ማቴሪያሎችንና መረጃዎችን ማግኘት ከመቻልዎ በተጨማሪ በሚመችዎት መርሃ ግብር ተፈትነው ካለፉ የምስክር ወረቀት ይቀበላሉ።

እንኳን ወደ ነሲሓ አካዳሚ የምዝገባ ገፅ መጡ!
ይህ ምዝገባ የሚቆየው እስከ ሚያዝያ 20/2011 ብቻ በመሆኑ አሁኑኑ ይመዝገቡ።
የምዝገባ ፎርሙን ለመሙላት ቢቸገሩ በዚሁ ፔጅ የሚገኘውን የማሳያ ቪዲዮ ይመልከቱ