ስለ እኛ

"ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም!" በሚል መሪ ቃል ሙስሊሙን ማህበረሰብ ለመሰገልገል በ2018 መባቻ በሙከራ ስርጭት ለአየር የበቃ የቴሌቭዥን ጣቢያ ሲሆን፤ ሙሉ በሙሉ ሸሪዓዊ እውቀትን መሰረት ያደረጉ የዳእዋ እና የትምህርት ፕሮግራሞች ይቀርቡበታለ። ከኪታብ ቂራአት ደርሶች በተጨማሪ በጣቢያው ከሚተላለፉት ፕሮግራሞቹ መካከል፤ ተውሂድ የነብያት ጥሪ፣ የታላቆች ታላቅ፣ የኑህ መርከብ እና ሌሎች ቤተሰባዊ እና ማህበራዊ አጀንዳዎችን የሚዳስሱ በርካታ ፕሮግራሞች አሉት። የርቀት ትምህርት አሰጣጥ መንገዶችን መሰረት በማድረግ ተማሪዎችን በሰርተፊኬት እና በዲፕሎማ የሚያስመርቀው ነሲሓ አካዳሚም የጣቢያውን አስፈላጊነት በእጅጉ ያጎላዋል። አላህ ለኡማው ጠቃሚ ያድርገው ዘንድ እንለምነዋለን።

የጣቢያው አስተዳደር