ነሲሓ ቲቪ ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም !!
ሰኞ, ኖቬምበር, 17, 2025
  • ነሲሓ ቲቪ ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም !!
  • ነሲሓ ቲቪ ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም !!
  • ነሲሓ ቲቪ ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም !!

ወደ ነሲሓ ቲቪ እንኳን በደህና መጡ

ኢብኑ መስኡድ ኢስላሚክ ሴንተር ከ1980ዎቹ ጀምሮ በተለያዩ  ዘርፍ ብዙ እና ሰፊ የዳዕዋ እንቅስቃሴዎች ከፍተኛ ድርሻ የነበራቸው ዱአቶች ስራዎችን በተቋም መልክ ለማቋቋም በሰኔ ወር 2001 ዓ.ል በሀገር ውስጥ የዲን ትምህርት ተቋማት እውቀት ቀስመው በዳእዋ ላይ በሚንቀሳቀሱ ዱአቶች እና በተለያየ ሀገር ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲዋች ተመርቀው ወደ ሀገራቸው በተመለሱ ወንድሞች  ጥረት ተመስርቶ በተቀናጀ መልኩ ለሙስሊሙ ሕብረተሰብ ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ የሚገኝ ተቋም ነው። ማዕከሉ በሀገራችን ኢስላማዊ ዳዕዋ ላይ ጉልህ በጎ አሻራ ከማስፈሩም በላይ ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ከመወጠን አንስቶ እስከ ማስፈጸም ሒደት ተጨባጭ ስራዎችን ማከናወን ችሎዋል። ከእነዚህ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ ነሲሓ ቲቪ ይገኝበታል።

ነሲሓ ቲቪ "ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም!" በሚል መሪ ቃል ሙስሊሙን ማህበረሰብ ለማገልገል በ2018 መባቻ በሙከራ ስርጭት ለአየር የበቃ የቴሌቭዥን ጣቢያ ሲሆን፤ ሙሉ በሙሉ ሸሪዓዊ እውቀትን መሰረት ያደረጉ የዳእዋ እና የትምህርት ፕሮግራሞች ይቀርቡበታለ። ከኪታብ ቂራአት ደርሶች በተጨማሪ በጣቢያው ከሚተላለፉት ፕሮግራሞቹ መካከል፤ ተውሂድ የነብያት ጥሪ፣ የታላቆች ታላቅ፣ የኑህ መርከብ እና ሌሎች ቤተሰባዊ እና ማህበራዊ አጀንዳዎችን የሚዳስሱ በርካታ ፕሮግራሞች አሉት። የርቀት ትምህርት አሰጣጥ መንገዶችን መሰረት በማድረግ ተማሪዎችን በሰርተፊኬት እና በዲፕሎማ የሚያስመርቀው ነሲሓ አካዳሚም የጣቢያውን አስፈላጊነት በእጅጉ ያጎላዋል። አላህ ለኡማው ጠቃሚ ያድርገው ዘንድ እንለምነዋለን።

ምን እናቀርባለን?

40+

መምህራን

10+

ቋንቋዎች

20+

ፕሮግራሞች

2000+

ርዕሶች

15+

ሰራተኞች